የውክልና እና የተለያዩ ሰነዶችን ማረጋገጥ

እባክዎ አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነፎቶ ኮፒ አያይዘው ይላኩ፡፡

 • ማንኛውም የውክልና ሰነድ እና ሌሎች ከብራዚል እና ሌሎች ሚሲዮኑ ተወክሎ ከሚሰራባቸው የላቲን አሜሪካ አገራት መንግስት የመነጨ (የተሰጠ) ዶክመንቶችን (ለምሳሌ - ውክልና፣ ያላገቡ መሆነዎትን የሚያረጋግጥ፣  የልደት የምስክር ወረቀት እና የመሳሰሉትን) ለማረጋገጥ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሄድ ዶኩመንቱን ማረጋገጥ ወደ ኤምባሲያችን መላክ ይኖርበታል፡፡

 • ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ዶኩመንት ከኢትዮጵያ የመነጨና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ከሆነ በቀጥታ ወደ ኤምባሲያችን በመላክ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ

 • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው የፖስታ አገልግሎት መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብዎትም፡፡  

ጠቅልለው ወደ አገር ቤት ሲገቡ በግል መገልገያ ዕቃዎች መመሪያ ቁጥር 51/2010 መሰረት እቃዎች ለማስገባት ለሚፈልጉ አመልካቾች

እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶ ኮፒያቸው አያይዘው ይላኩ፡፡

 •  አገልግሎቱን ለመጠየቅ አምስት አመትና ከዚያ በላይ በውጭ አገር የኖሩ መሆን ይኖርብዎታል፡፡ በአምስት አመት ውስጥ ከአንድ ግዜ በላይ አገልግሎቱን መጠየቅ አይችሉም።

 • ወደ አገር ቤት ያለ ቀረጥ እና ቀረጥ ከፍለው ማስገባት የሚችሉትን ዕቃዎች ዝርዝር  (ለማግኘት ይህን ይጫኑ)

 • ቀረጥና ታክስ ተከፍሎበት እና ካለቀረጥና ታክስ የሚገባ የዕቃ ዝርዝር መግለጫ ፎርም እዚህ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።  (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ይህን ይጫኑ)

 • ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው የፖስታ አገልግሎት መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ያረጋግጡ፡፡

 

አገልግሎቱ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ

 • አምስት አመትና ከዚያ ላይ በውጭ አገር መቆየትዎን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ (የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ወይም ሌላ ማስረጃ)

 • ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ አገልግሎቱ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ በሁለት ኮፒ

 • በብራዚል (እና ሚሲዮኑ ተወክሎ ከሚሰራባቸው የላቲን አሜሪካ አገራት) ነዋሪ መሆንዎን የሚያሳይ ማስረጃ በሁለት ኮፒ (የውጭ ሀገር ዜጋ ላልሆኑ)

 • የውጭ ሀገር ዜግነት የወሰዱ ከሆነ አገልግሎቱ ያላበቃ የብራዚል (ወይንም ሚሲዮኑ ተወክሎ ከሚሰራባቸው የላቲን አሜሪካ አገራት) ፓስፖርት ሁለት ኮፒ አያይዞ መላክ

 • መጠየቂያ ቅጽ መሙላት (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ይህን ይጫኑ)

 • አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ አብሮ መላክ

Our Visa account 
Embaixada da Republica Democratica Federativa da Etiopia

Name of the Bank - Banco do Brasil

Bank code: 001

Agency - Agência: 1606-3

Account Number - Conta Corrente: 73-391-1 

SWIFT CODE (BRASILIA)-BRASBRRJBSA (only for those outside Brazil*)

IBAN CODE: 001160630000674761 


* If the applicants are from outside Brasilia they must deposit $20:00 dollar more for bank service charge. 

 
 

Engage with Us on 

 • Facebook
 • Twitter

SHIS - QI 7, Conjunto 4, Casa 9 – Lago Sul CEP 71615-240 Brasília - Distrito Federal

ethiobrazil@ethiopianembassy.org.br / +55  (61)  3248-0361