የኢትዮጵያ ፓስፖርት

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ማሳሰቢያ

 •  አስፈላጊ ማስረጃዎችን አለማሟላት የአገልግሎት መስጫ ጊዜውን ሊያራዝም አልያም ፋይልዎ ተመላሽ ተደርጎ እንደ አዲስ ማመልከት ሊጠበቅብዎት ይችላል። 

 •  በኢምባሲያችን በኩል የሚያመለክቱት የፓስፖርት ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው አገር ቤት ተልኮ በመሆኑ ከጉዞዎ/ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ ከ45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡ 

 • ፓስፖርትዎ ተዘጋጅቶ እስከሚደርስዎ ድረስ መቆየት የማይችሉና በተለያየ አጣዳፊ ምክንያቶች በአስቸኳይ ወደ አገር ቤት መሄድ ከፈለጉ ወደ አገር ቤት ለመግቢያ ብቻ የሚያገለግለውን ሊሴ ፓሴ  (የሊሴ ፓሴ አገልግሎት የሚለውን ይክፈቱ) ወስደው ከአገር ቤት ፓስፖርት ማመልከት ይችላሉ።

 • የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ ጉዞዎ ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ ከኢሚግሬሽን ፓስፖርትዎን መረከብ ይችላሉ።

 • ኢምባሲው ፓስፖርትዎን ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ እባክዎ በተነገረዎት በሳምንት ግዜ ውስጥ ማስረጃውን ይላኩልን፡፡ ሆኖም ማስረጃውን እንዲልኩ ለ3ኛ ጊዜ ተገልጾልዎት ከሆነና በወቅቱ ላቀረቡ ፋይልዎ ተመላሽ ተደርጎ እንደ አዲስ ማመልከት ይጠበቅቦታል፡፡

 •  ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው የፖስታ አገልግሎት መሆን ይገባዋል፡፡ የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ የተዘጋጀለዎት ሰነድ ወደ እርሶ ተመላሽ ለመደረጉ ባለዎት የፖስታ Tracking Number በመጠቀም ማጣራት ሰለሚችሉ ይህንኑ መረጃ ለማረጋገጥ ወደ ኢምባሲው መደወል አይጠበቅብዎትም፡፡  የተዘጋጀለዎትን ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን በተረከብንበት እለት በሚልኩልን የመመለሻ ፖስታ ወደ እርሶ ይላካል፡፡

የአገልግሎት ክፍያ - በባንክ ዲፖዚት ወይንም በጥሬ ገንዘብ መክፈል ይችላሉ።

Embassy's address: SHIS - QI 7, Conjunto 4, Casa 9 – Lago Sul CEP 71615-240

Brasília - Distrito Federal - Brasil

Our Visa account:  Embaixada da Republica Democratica Federativa da Etiopia

Name of the Bank - Banco do Brasil

Bank code: 001

Agency - Agência: 1606-3

Account Number - Conta Corrente: 73-391-1 

SWIFT CODE (BRASILIA)-BRASBRRJBSA (only for those outside Brazil*)

IBAN CODE: 001160630000674761 

​​

Download Application Form

Issuance of New Passport and Renewal of old Passport Fee

የአገልግሎት ክፍያ

  • ፓስፖርቱ የጠፋብዎት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ  ለባለ 32 ገጽ ፓስፖርት $90; $165 ለባለ 64 ገጽ ፓስፖርት

  • ፓስፖርቱ  የጠፋብዎት ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ ለባለ 32 ገጽ ፓስፖርት $120 ለባለ 64 ገጽ ፓስፖርት $220

  • ፓስፖርቱ የጠፋብዎት በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ እና ከዚያ በላይ ጊዜ ከሆነ ለባለ 32 ገጽ ፓስፖርት $180 ለባለ 32 ገጽ ፓስፖርት$330

 
 

Engage with Us on 

 • Facebook
 • Twitter

SHIS - QI 7, Conjunto 4, Casa 9 – Lago Sul CEP 71615-240 Brasília - Distrito Federal

ethiobrazil@ethiopianembassy.org.br / +55  (61)  3248-0361