የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ አገልግሎት 

በትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች ከትውልድ ሀገራቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር በትውልድ አገራቸው የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል፡፡  

የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች በጥቂቱ፤

 • ወደ ኢትዮጵያ ለመግባትና ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየትም ሆነ ለመኖር የመግቢያ ቪዛና የመኖርያ ፈቃድ እንዲኖረው አይጠየቅም።

 • ከአገር መከላከያ፣ የአገር ደህንነትና ውጭ ጉዳይ የመሳሰሉ የፖለቲካ መ/ቤቶች በስተቀር የስራ ፈቃድ እንዲያወጣ ሳይገደድ በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥሮ መስራት ይችላል፡፡

 • እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት መቆጠር ከፈለገ በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ሕግ መሰረት ለአገር ውስጥ ባለሀብት በተፈቀዱ የኢንቨስትመንት መስኮች መሳተፍ ይችላል፡፡

የኢትዮጵያ ተወላጅ መሆኑን የሚገልፅ መታወቂያ ካርድ የተቀበለ የውጭ ዜግነት ያለው ሰው ቤተሰቦች (የሌላ አገር ዜግነት ያለው ባል፣ ሚስት ወይም ልጅ) ይህንኑ የሚገልፅ የመታወቂ ካርድ የማግኘት ሙሉ መብት አለው፡፡

የውጭ አገር ዜግነት የያዘ የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያውን የሚያገኘው የኢትዮጵያ ተወላጅ በመሆኑ ብቻ እንደ መብት ተቆጥሮ ሳይሆን አመልካቹ ለወገኖቹ የኑሮ መሻሻል ለትውልድ ሀገሩ እድገትና ብልፅግና የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ሲታመንበት ይሆናል፡፡

 

የተወላጅነት መታወቂያ ለማግኘት የሚቀርቡ ከውጭ አገር የመነጩ የተለያዩ ማስረጃዎች (ከውጭ አገር የተሰጠ የልደት ምስክር ወረቀት፣ የጋብቻ ማስረጃ ወዘተ) በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተተረጎሙና ከዚያም ስለትክክለኛነታቸው በብራዚል (ወይንም ሚሲዮኑ ተወክሎ በሚሰራባቸው የላቲን አሜሪካ አገራት) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

 

አካለ መጠን ላልደረሱ የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጆች ስለሚሰጥ አገልግሎት 

 

በወላጅ አማካይነት መታወቂያውን ለመውሰድ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

 • የወላጅ የኢትዮጵያ ተወላጅነት የሚያረጋግጥና  ስም ከነአያት ያለው ዶክመንት (መታወቂያ ካርድ፤ ፓስፖርት…)

 • የልጁ/ጅቷ የተረጋገጠ ሕጋዊ የልደት ምስክር ወረቀት

 • የልጁ/ጅቷ አገልግሎቱ ቢያንስ ስድስት ወር የፀና ፓስፖርት፤

 • (3*4) መጠን  ያለውና ቢያንስ  ከ6ወር ወዲህ የተነሱት 4 ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)

 • በሁለት ቅጂ ማመልከቻ ቅፅ መሙላት (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ይህን ይጫኑ)

 • ዕድሜያቸው 14 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ልጆች በኤምባሲው በመገኘት አሻራ መስጠት

 • የአገልግሎት ክፍያ ለማወቅ (ይህን ይጫኑ)

                

የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እርማት

 • በሁለት ቅጂ ማመልከቻ ቅፅ መሙላት፤ (መጠየቂያ ቅፅ ለማግኘት ይህን ይጫኑ)

 • እርማት የሚደረገው የመታወቂያ ካርዱ ባለቤት የሚፈልገውን እርማት ጠቅሶ ሲያመለክትና እርማቱን ማድረግ ስለማስፈለጉ አሳማኝ ምክንያት በበቂ ማስረጃ በማስደገፍ ማቅረብ

 • እርማቱ የስም ለውጥ ከሆነ ስልጣን ከተሰጠው ፍርድ ቤት የተሰጠና አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ ዋናው ከሁለት ቅጂ ጋር፣ ወይም በጋብቻ ምክንያት የስም

 •  ለውጥ ከሆነ አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ የጋብቻ ማስረጃ ፣ እንዲሁም የስም ለውጥ በጉዲፈቻነት ከሆነ አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ ሕጋዊ የሰነድ ማስረጃ ዋናው ከሁለት ቅጂ ጋር ማቅረብ

 • እርማቱ የተጠየቀው በጋብቻ ምክንያት በተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆነ የውጭ አገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ የመታወቂያ ካርድ ላይ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ ሁለት ቅጂ (ቅፅ ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)፣ እንዲሁም አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ከሁለት ቅጂ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ፤

 • አሻራ ያልሰጡ እድሚያቸው 14 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው አመልካቾች አሻራ መስጠት ይኖርባቸዋል፤

 

የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥበት የጊዜ ገደብና የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት

 • አገልግሎቱን ለማግኘት ሲያመለክቱም ሆነ ሲረከቡ በአካል ወደ ኤምባሲ መቅረብ የለብዎትም። በመሆኑም በፖስታ ቤት በኩል ብቻ ተረክበን የምናስተናግድዎ በመሆኑ ወደ ኤምባሲው ሲልኩም ሆነ የተዘጋጀልዎትን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ወደ እርሶ መልሰን ለመላክ Tracking Number ባለው ፖስታ አያይዘው ይላኩ። ኤምባሲው መታወቂያ ካርድዎ ከኢትዮጵያ እንደተረከበ በተቻለ ፍጥነት በላኩልን መመለሻ ፖስታ ይልክልዎታል። የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱም ሆነ ወደ እርሶ ለመመለሱ ባለዎት Tracking Number በመጠቀም ማወቅ ስለሚችሉ ወደ ኤምባሲ መደወል አይጠበቅብዎትም።

 • የመታወቂያ ካርዱ እንዳይሰጥ የሚወሰን ከሆነ ምክንያቱ ለአመልካቹ በፅሁፍ ሊገለፅ ይገባል፡፡ አመልካቹ በተሰጠው ወሳኔ ቅሬታ ካለው እስከ ሚስዮኑ መሪ ወይም ኢሚግሬሽን ዳይሬክተር ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል፤ አመልካች በፅሑፍ የሚያቀርበውን ቅሬታ ሚስዮኑ ተቀብሎ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም ኢሚግሬሽን/ ለብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ይልክለታል ወይም በራሱ በኩል በቀጥታ ለተቋማቱ ያቀርባል፡፡

 • የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርዱ ለ5 አመት የሚያገለግል ይሆናል፡፡ እባክዎ የመታወቂያ ካርዱ አገልግሎት ዘመን ሳያበቃ መታወቂያ ካርዱን ያሳድሱ፡፡

 • የአገልግሎት ዘመኑ እስካላበቃ ድረስ  መታወቂያ ካርዱን በመያዝዎ ያለ ቪዛ ኢትዮጵያ ገብተው መውጣት ይችላሉ፡፡

 • የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀደም አዲሱን Machine Readable የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሲወስዱ የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡

 • እባክዎ ከጉዞዎ ወይም ከታደሰ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ጋር በተያያዘ አገልግሎት ከመጠየቅዎ ቢያንስ ከ45 ቀናት አስቀድመው ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡

 • ኢምባሲው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ እባክዎ በተነገረዎት በሳምንት ጊዜ ውስጥ ማስረጃውን ይላኩልን፡፡ ሆኖም ማስረጃውን እንዲልኩ ለ3ኛ ጊዜ ተገልጾልዎት ከሆነና በወቅቱ ካላቀረቡ ፋይልዎ ተመላሽ ተደርጎ እንደ አዲስ ማመልከት ይጠበቅብዎታል፡፡

 

Engage with Us on 

 • Facebook
 • Twitter

SHIS - QI 7, Conjunto 4, Casa 9 – Lago Sul CEP 71615-240 Brasília - Distrito Federal

ethiobrazil@ethiopianembassy.org.br / +55  (61)  3248-0361